SNNPRS-BOSIT
በመድረኩ የክልል ሴክተር ቢሮ ኃላፊዎች ፣የዞንና የልዩ ወረዳ የተቋሙ መምሪያ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በተያዘው መርሃ-ግብር መሰረት የተቋሙ የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡
የድጋፉ ዓላማ የቴክኖሎጂ ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን በማስፋት የቪድዮ ኮንፈረንስ አገልግሎቶች ሳይቆራረጡ የምስልና የድምጽ ጥራት ባለው መንገድ እንዲተገበሩና ዞኖች መዋቅሮቻቸውን ጊዜ፣ ወጪ እና ጉልበትን በቆጠበ መልኩ ምልልስ በማስቀረት መደገፍ እንዲችሉ ለማስቻል መሆኑን የቢሮው ዋና ኃላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ ገልጸዋል፡፡
በሳይንስና ተክኖሎጂ ዘርፍ የፈጠራ ስራ የሚሞክሩትን ስናበረታታ የሚችሉ ይፈጠራሉ በሚል መሪ ቃል የዲላ ዩኒቨርስቲ እስቴም ማዕከል ከጌዴኦ ዞን ትምህር መምሪያ እና ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመተባበር የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽንና ፓናል ውይይት በዲላ ከተማ አካሂዷል።
በመርሃ-ግብሩ የተገኙ የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሳይንስ ፈጠራ ስርጸት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙሂዲን ሁሴን ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት ተግባራዊ ማድረግ የሚቻሉባቸው በቂና ምቹ የሆነ ምህዳር መፍጠር ከሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የሚጠበቅ እንደሆነና ሳይንስና ተክኖሎጂ በዘላቂነት ውጤታማ ሆኖ እንድቀጥል የተጠናከረ እውቀትና ዝንባለ ያለውን ትውልድ መፍጠር እንደምያስፈልግ ተናግረዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሁሉለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ እንደሆነ የገለጹት ኃላፊ በዘርፉ ለተጠቃሚዎች ዕድገት ሊያበረክት የሚችለውን አስተዋጽኦ በሚገባ ለመጠቀም የሚያስችሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ…Read More
የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኢኮቴ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መንግስቱ በየነ አዲስ የኢኮቴ ኢንኩቤሽን ማዕከል እየተቋቋመ ከሚገኝባቸው ዞኖች ( ወላይታ፣ሀዲያ እና ጋሞ ) የመምሪያ ኃላፊዎች ጋር አስፈላጊው ሙሉ ዝግጅት ተጠናቆ ማዕከላቱን ስራ ማስጀመር ስለሚቻልበት ሁኔታ በቨርቿል ውይይት አድርገዋል፡፡
አቶ መንግስቱ በውይይቱ እያንዳንዱ ዞን ከክልል በተደረገልት የቁሳቁስ ድጋፍ መሰረት ምቹ የሰራ ቦታ ማመቻቸት ፣ ኔትወርክ መዘርጋት እና ስራ አጥ ወጣቶችን የመመልመል ስራ ማከናወን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የኢኮቴ ኢንኩቤሽን ማዕከላቱን የማቋቋም ዓላማ ስራ አጥ ወጣቶችን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ማለትም በኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገና፣ በሶፍት ዌር ልማት እና በኔትወርክ ዝርጋታና ልማት ዘርፍ ገበያው ላይ ተወዳዳሪና ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ለወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር በመሆኑ ዞኖቹ በአፋጣኝ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው በቅርብ ቀን ወደ ስራ እንዲገቡ አሳስበው ውይይቱ በተነሱ…Read More
የዌብ ፖርታል ልማት በከተማችን እንዲጀመር የፌዴራል ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ቢሮ ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸውን የተናገሩት የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ ናቸው።
አክለውም ከንቲባው በከተሞች የዌብ ፖርታል መልማት በኢኮኖሚና ማህበራዊ ትስስር፣ ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ ለመፍጠርና የየከተሞችን አጠቃላይ መረጃ ህብረተሰቡ በማንኛውም ቦታና ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እንዲከታተል ትልቅ ሚና እንዳለውም ገልፀዋል።
የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማፋጠንና በዲጂታል ቴክኖሎጂ እየተካሄደ ያለውን አለም አቀፍ ውድድር በሁሉም መስክ ተፈላጊና ተመራጭ የሆነ ከተማን መመስረትን አላማ በማድረግ የዌብ ፖርታል ልማት ላይ ክልሉ ትኩረት ማድረጉን በምስረታ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገበሬ ጋጌ ተናግረዋል።
በተከፈተው ዌብ ፖርታል መረጃዎች ተጠናክሮ በመደራጀታቸው አበረታች መሆኑን ገልፀው በቀጣይም መረጃዎችን ወቅታዊ በማድረግ ከተማዋ…Read More
የኢትዮጵያን ህልውና ለማረጋገጥ መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሁለገብ ድጋፍ በማድረግ የዜግነት ግዴታን መወጣት እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለግሰዋል፡፡
"ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን!!" በሚል መርህ በመሥሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በተካሄደው የደም ልገሳ ሥነ ስርዓት ላይ በምክትል የቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የሳይንስና ስርጸት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙሂዲን ሁሴን ባደረጉት ንግግር የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሀገር ህልውና እየከፈለ ላለው መስዋዕትነት መላው ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የበኩላቸውን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠልና” ከሠራዊቱ ጎን በቁርጠኝነት መሰለፍ እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡
የቢሮውሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች ደማቸውን ለሠራዊቱ በመለገስ አጋርነታቸውን በተግባር ማስመስከራቸው ሀገራቸው የምትጠይቀውን ማንኛውንም ዓይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ቁርጠኛ መሆናቸውን ያሳያል ያሉት አቶ…Read More
Copyrights 2020. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU