• Call Us
  • +25146 2206572

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና ትንተና ዳይሬክቶሬት

የሚሰጡ አገልግሎቶች፡

  • ከባለድርሻ አካላት ጋር የምርምር የትስስር ፎረም/ምክር ቤት አንዲቋቋም ያደርጋል፤ ያስተባብራል፣ ይመራል፤
  • ምርምር ለማካሄድ ፕሮፖዛል እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ይገመግማል፤ ያፀድቃል፤ ለምርምሩ በጀት እንዲመደብ ያደርጋል፤ይከታተላል፤
  • የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ሳይንሳዊ ምርምሮች እንዲካሄዱና የተገኙት የምርምር ውጤቶች እንዲሸጋገሩ ያደርጋል፤ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ይደግፋል፤
  • ኢንዱስትሪዎች፤ አርሶአደሮች፤ ኢንተርፕራይዞች፤ የምርት ጥራትና ምርታማነታቸውን በማሻሻል ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለማቅረብ የሚያስችል የምርምርና ኢኖቬሽን ስራን ይመራል፣ ይደግፋል፤
  • የፖሊሲ ሀሳቦችን ያመነጫል፣ ኢንዱስትሪዎችና ኢንተርፕራይዞች ሊከተሉት የሚገባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የመቅዳት ስትራቴጂዎችን ይለያል፣ ያወጣል፣ ይገመግማል፣
  • ለምርምር ውጤቶች የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት ካስፈለገ እንዲዘጋጅ ሀሳብ ያቀርባል፣ ያዘጋጃል፣ ይገመግማል፣ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤
  • የክልሉን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት እንዲካሄድና የተደራጀ መረጃ እንዲኖር ያስተባብራል፤ ይደግፋል፤
  • በጥናት የታዩ ክፍተቶችን መሰረት በማድረግ የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት ካስፈለገ እንዲዘጋጅ ሀሳብ ያቀርባል፣ ያዘጋጃል፣ ይገመግማል፣ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤
  • የተሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎችና የምርምር ውጤቶች በህብረተሰቡ ውስጥ ያመጡትን ፋይዳ በዳሰሳ ጥናት የመለየትና ግብረመልስ የመስጠት ስራን ይመራል፤ ያስተባብራል፤