• Call Us
 • +25146 2206572

የጨረራ ኢንስፔክሽንና የጥራት መሠረተ ልማት ዳይሬክቶሬት

የሚሰጡ አገልግሎቶች፡

 • የጨረራ አመንጪ መሳሪያዎችን በመለየትና በመከታተል ህብረተሰቡ ካስከፊ ጉዳት ፣ እንዲጠበቅ ይደረጋል፤
 • በአገልግሎት ላይ እየዋሉ ያሉ መሳሪያዎች የካሊብሬሽን ስራ ማከናወናቸዉን የማረጋገጥ ሥራ ይሠራል፤
 • ምርቶችና አገልግሎቶች የጥራት ደረጃቸውን ስለማሟላታቸው ከሚመለከተዉ አከላት ጋር በትብብር በመስራት አግባብ ያለው ሙያዊ አገልግሎት መስጠቱን ያረጋግጣል፣
 • በጥራት እና ደረጃዎች ዙሪያ የተለያዩ የአህዝቦት ስራዎች እንዲካሄዱ ያደረጋል፣
 • የክልሉ ህብረተሰብ ከባህላዊ መመዘኛዎች ወደ ዘመናዊ አለካክ እንዲለወጥ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል፡፡
 • የህክምና ተቋመት፤በኢንዱስትሪዎች፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣ቤተሙከራዎችና በምርምር ተቋማት መካከል ጠንካራ ትስስርና ትብብር እንዲፈጠር ሁኔታዎችን በማመቻቸት የጨረራ ኢንስፔክሽንና የጥራት መሠረተ ልማት ስራ በትብብር እንዲሰራ ይደረጋል ፤
 • በሬዲዮ አክቲቭ ኬሚካል የሚገለገሉ ቤተሙከራዎች፣ምርምር ማዕከላት፣ህክምና ማዕከላት እና ኢንዱስትሪዎችን ለመከታተል የሚያግዙ መሳሪያዎች እንዲጠቀሙ/እንዲያስገቡ በማድረግ ብክለትን ማስወገድ እና ብክለት በሚያጋጥምበት ጊዜ አስቸኳይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል አሰሪር እንዲሰፍን ይደረጋል፡፡
 • የጨረር አመንጪ መሳሪያዎች እና የሬዲዮ አክቲቭ ቆሻሻ ጨረር አመንጪ ኬሚካሎች ክልላዊ ዳታ ቤዝ እንዲኖር ይደረጋል፡፡
 • የሥነ-ልክና አክሪዲቴሽን ሥራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተጠናከረ መልኩ ይሠራል፡፡
 • በክልሉ የሚመረቱ ምርቶችና የሚሰጡ አገልግሎቶች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁና የተስማሚነት ምዘና በማድረግ ተወዳዳሪነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን ይደርጋል
 • የጨረራ አመንጪ መሣሪያዎች ጥቅምና ጉዳት የተስማሚነት ምዘና የጥራት ማረጋገጫ ጠቀሜታ ለተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት ተከታታይ የሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ይሠጣሉ፡፡
 • በፈቃድ መስጠት እና ኢንስፔክሽን ወቅት ለሚሰጥ አገልግሎት ከክፍያ ነጻ በማድረግ ከጨረር ጋር የተያያዘ ቴክኖሎጂ በሰፊው ወደ ክልላችን እንዲገባ ማድረግ እና ጨረር ነክ ኢንዱስትሪዎችን ማበረታታት ይገባል፡፡
 • ህብረተሰቡ በተደጋጋሚ የሚገለገልባቸው መሳሪያዎች ለምሳሌ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ማይክሮዌቭ ምድጃ፣ የጀርም እና ፀረ ባክቴሪያ መሳሪያ፣ የሚመለከቱ አዲስ የምርምር ውጤት ተግባራዊ ያደረገ ወቅታዊ ማስረጃ/መረጃ በሚወጣበት ጊዜ ክትትል በማካሄድ መረጃውን ለህዝብ እንዲደረስ በማድረግ  ህብረተሰቡ ሳያስበው በድንገተኛ አደጋ እንዳይወድቅ ማድረግ፣
 • በዘመናዊ ሶፍትዌር እና ዳታ ቤዝ የተጠናከረ የቁጥጥር እና ኢንስፔክሽን ስርአት በመጠቀም ኢንስፔክተሮች ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጡበት ዘመናዊ አሰራር ይፈጠራል፡፡
 • ፈቃድ በሚሰጥበት ወቅት ለሚሰጠው የኢንስፔክሽን አገልግሎት የሚጠየቅ ክፍያ፡-የመሳሪያዎች ብዛት፣የመሳሪያ አይነት፣የቦታ ርቀት፣የአካባቢ አየር ፀባይ፣ለስራው የሚመደቡ ባለሙያዎች የስራ ሂደቱን መሰረት ያደረገ እንዲሆን በማድረግ የወጪ ፍትሃዊ ክፍፍል እንዲካሄድ በማድረግ ከመንግስት ካዝና አላስፈላጊ ወጪ እንዲይወጣ ይደረጋል፣፡