በዕለቱ በነበረው መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ዋና ኃላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ የውይይት መድረኩ የተፈጠረው ጉድለታችንም ሆነ ስኬታችን የጋራ በመሆኑ በበጀት ዓመቱ ከነበሩ ስኬቶች መልካም ተሞክሮን ለመቅሰም እንዲሁም ከጉድለቶቻችን መሻሻልን ለማምጣት ሁሉም የተቋም ሠራተኛ ባለቤት በመሆኑ በቀጣይ በጀት ዓመት ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅኦ ለሴክተሩ ግብ ስኬት የድርሻውን እንዲወጣ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል። በልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ከምባታ ካዌ የተቋሙ የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ሪፖርትና የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የተቋሙ ሠራተኞችም መድረኩ ተቋማቸውን በጥልቀት እንዲረዱና በየዘርፋቸው የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ግንዛቤ የፈጠረላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
የ2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም ከዚህ ቀደም ከነበረው በእጅጉ የላቀ መሆኑ ተገምግሟል።
በ2014 በጀት ዓመት ከዘንድሮ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መሥራት እንዳለብን የቢሮው ኃላፊ አሳስበው ለዚህም ስኬት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈው የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።
Copyrights 2020. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU