ባላደጉ ሀገራት የኢኮኖሚ ውድቀት አንዱ ምክንያት ያላግባብ የሚባክን ጊዜ ነው ያሉት የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ አንድ ጉዳይ ለማስፈፀም ሁለት ቀንና ከዚያ በላይ ጊዜን እናቃጥላለን ይህ ደግሞ ያለ ስራ ማሳለፋችን ብቻ ሳይሆን ለተጨማሪ ብክነትም እየዳረገን ነው ብለዋል።
ባለፈው አመት የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ተቋማት ስራዎቻቸውን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ኢንዲሆን ለማድረግ ባደረገው ጥረት በክልል ፣ዞንና ወረዳ ተቋማት በኔትወርክ በማስተሳሰር እንዲሁም ለባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት የተሻለ ውጤት መመዝገብ ተችሏል ብለዋል።
ቴክኖሎጂን በትውልድ ውስጥ ለማስረፅ ቢሮው በክልሉ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የአይሲቲ ሴንተር ( የሳይንስ ከበባት)ለመክፈት ጥረት አድርጓል ያሉት አቶ ገብሬ ይህም አዲሱን ትውልድ ከቴክኖሎጂ ጋር ለማቀራረብ ያግዛል ብለዋል።
Copyrights 2020. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU