• Call Us
  • +25146 2206572

የተማሪዎች የፕሮጀክት ስራ (በጀት ማኔጅመንት ሲስተም) ተገመገመ፡፡

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት  ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ  ቢሮ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ባደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት መሠረት  በክልሉ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ለተግባር ልምምድ የሚወጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የተማሪዎችን ክህሎት በተግባር ስልጠና እያጎለበተ ይገኛል፡፡ 
በዚሁ መሠረት ከሀምሌ 01/2014ዓ.ም ጀምሮ ለተግባር ልምምድ /አፓረንት ሽፕ/ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተቀበላቸው ተማሪዎች ከፍተኛ የዘርፉን ባለሙያዎች በመመደብ ድጋፍ ሲያደርግላቸው ቆይቷ፡፡ በተግባባር ልምምዳቸው ወቅት ተማሪዎቹ እንድያለሙ የተሰጣቸውን የበጀት ማኔጅመንት ሲስተም ፕሮጀክት አጠናቀው አስገምግመዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በተቋሙ ከፍተኛ የሲስተም ባለሙያዎች አጠቃላይ ይዘቱ ተገምግሞ በጥንካሬ እና በጉድለት አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡ ተማሪዎቹም በቀጣይ የተሰጣቸውን አስተያየት እንደ ግብአት በመጠቀም ሲስተሙን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እና አገልግሎት ላይ እንዲውል ለማድረግ እንደ ሚሰሩ ገልጸው ተቋሙ ላደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በተቋሙ ውስጥ ተማሪዎችን ተቀብሎ የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ የሚያደርገው የግል ሥራ ፈጠራ ማዕከላት አገልግሎትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ መስፍን ግርማ እንደገለፁት  የዚህ ተግባር ዋና ዓላማ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በንድፈ ሀሳብ ይማሩት የነበረን ትምህርት በተግባር ልምምድ እንዲያዳብሩ ማስቻል  በመሆኑ ተማሪዎች ለተግባር ልምምድ የተመደቡበትን ጊዜ ሳይሸራርፉ በመጠቀም በቂ ዕውቀት መጨበጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡