የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ባደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት መሠረት በቴክኖሎጂው ዘርፍ ለተግባር ልምምድ የሚላኩ ተማሪዎችን ተቀብሎ የተማሪዎችን ክህሎት በተግባር ስልጠና እያጎለበተ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሠረት ለተግባር ልምምድ /አፓረንት ሽፕ/ የመጡት የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተቋሙ በነበራቸው የይቆታ ጊዜ ሲያለሙት የነበረ የዳታ ቤዝ /የመረጃ ቋት/ የመጀመሪያ ዙር ግምገማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስርፀት ዘርፍና የቢሮው ም/ኃላፊ፣የስራ ክፍል ዳይሬክቶሬቶች እና ከፍተኛ የዘርፉ ባለሙያዎች የተገመገመና አስተያየት የተሰጠበት ሲሆን በሁለተኛዙር የግምገማ ሂደት ተማሪዎቹ የተሰጣቸውን አስተያየት እንደ ግብዓት በመጠቀም ተሻሽሎ የለማ የዳታ ቤዝ ሲስተም አቅርበው አስገምግመዋል፡፡
በቀጣይም ተማሪዎቹ በመልማት ሂደት ላይ የሚገኘውን ሲስተም ከፍጻሜ ለማድርስ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው እና ወደ ዩኒቨርሲቲያቸው ሲመለሱ ከመምህራኖቻቸው ጋር በመቀናጀት ጅምር ስራውን እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በመጨረሻም የግል ሥራ ፈጠራ ማዕከላት አገልግሎትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ መስፍን ግርማ እንደገለፁት የተግባር ልምምዱ ዋና ዓላማ ተማሪዎች በቲዎሪ ይማሩት የነበረን ትምህርት በተግባር ልምምድ በማዳበር ተጨባጭ ዕውቀት እንዲያገኙ ማስቻል ነው፤ ብለዋል፡፡ አክለውም እነዚህ ተማሪዎች ከዜሮ በመነሳት (በቲዎሪ ብቻ ከሚያውቁት ተነስተው) በተደረገላቸው ድጋፍና ክትትል ይህንን መስራታችሁ ለነገም የሀገር ተስፋዎች ናቸውና ሊበረታቱና ሥራዎቻቸውን በማጎልበት ቴክኖሎጂውን አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ሥራ መስራት
Copyrights 2020. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU