• Call Us
 • +25146 2206572

የመረጃ መረብና ሶፍትዌር ልማት ዳይሬክቶሬት

የሚሰጡ አገልግሎቶች

 • ውስብስብ  የሆነ እና ያልሆነ የመረጃ መረብ ዝርጋታ ማድረግ        
 • ውስብስብ  የሆነ  እና ያልሆነ የሶፍትዌር /ረ-ገጽ/ ልማት ማካሄድና ስተማይዝ ማድርግ          
 • የመረጃ መረብና የሶፍትዌር ልማት ቴክኒካል ድጋፍ መስጠት        
 • የዲዛይንና ጥናት  እንዲሁም  ዝርዝር መለኪያ ማዘጋጀት        
 • የአይሲቲ ባለሙያዎች የቅጥር ፈተና ዝግጅት ማድረግ       
 • የብቃት ማረጋገጫ መረጃ ዝግጅት    
የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተገልጋዮች የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች
ውስብስብ  የሆነ እና ያልሆነ የመረጃ መረብ ዝርጋታ ማድረግ
 • የሚቀርበው ጥያቄ  በዝርዝር ዲዛይን ጥናት፣ ዕቅድናበበጀት የተደገፈ መሆን አለበት፡
 • የሚዘረጋለት ተቋም ስራውን ሊከታተልና ሊረከብ  የሚችል ባለሙያ ሊኖረው ይገባል፡
 • የአገልግሎት ጥያቄዉንም ሆነ ወጪውን ለመተካት  በደብዳቤ ማቅረብና ፕሮግራም ማስያዝ፣
ውስብስብ  የሆነ  እና ያልሆነ የሶፍትዌር /ረ-ገጽ/ ልማት ማካሄድና ስተማይዝ ማድ
 • በተቋማቸው የመረጃ መረብ መኖሩን ማረጋገጫ ማቅረብ፡፡
 • ጥያቄው በዕቅድና በበጀት የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
 • የተቋሙን አጠቃላይ  መረጃ የያዘ ሰነድ ማቅረብ
 • ስራውን የሚከታተልና የሚቆጣጠር እንዲሁም ተረክቦ ስራውን ሊያስቀጥል የሚችል ባለሙያ መመደብ

የመረጃ መረብና የሶፍትዌር ልማት ቴክኒካል ድጋፍ መስጠት  የዲዛይንና ጥናት  እንዲሁም  ዝርዝር መለኪያ ማዘጋጀት

 • ጥያቄውን በስልክ፣ በኢሜይል፣ ፋክስ ወይም በደብዳቤ ማቅረብ
 • የሚፈልጉትን ድጋፍና ምክር አገልግሎት ዓይነትና ስፋት በግልጽ ማሳወቅ
 • ጊዜ መወሰንና ቀድሞ ማሳወቅ
የአይሲቲ ባለሙያዎች የቅጥር ፈተና ዝግጅት ማድረግ
 • የአገልግሎት ጥያቄዉን በደብዳቤ ቀድሞ ማቅረብ

 

የብቃት ማረጋገጫ መረጃ ዝግጅት
 • የአገልግሎት ጥያቄዉን በን/ኢ/ከ/ል/ቢሮ/መምሪያ/ጽ/ቤት በኩል በደብዳቤ ማቅረብ
 • ጥያቄዉን በማመልከቻ  ማቅረብ
 • የአገልግሎት አይነቱን መግለጽ
 • መሟላት ሚገባቸዉን ሰነዶች በሙሉ አሟልቶ መቅረብ  ምሳሌ፡- የንግድ ምዝገባ ሰርተኬት፣ የግብር  ከፋይነት  መለያ ቁጥር /Tin number/ የትምህርት ማስረጃ፣ በውልና  ማስረጃ  የፀደቀ  የቤት ኪራይ  ውል ወይም  የቤት ካርታ ፕላን ኮፒ፣ መታወቂያና ሁለት ጉርድ  ፎቶ፣ ማህበር  ከሆነ  የመመስረቻ  ፅሁፍና  መተዳደሪያ ደንብ  እንዲሁም እንደ  ንግድ መስኩ  የሚያስፈልጉ  ቁሳቁሶች ወዘተ