• Call Us
  • +25146 2206572

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ት ሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ

SNNPRS-BOSIT

የቢሮው አጠቃላይ ገጽታ

ባለፉት ዓመታት በክልላችን የሰላም፣ የዲሞክራሲና የልማት ተግባሮች ለማከናወን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ተነደፈው  በብቃት ሊያስፈጸም የሚችል አቅም የተሟላ ሊሆን ባለመቻሉ ከክልል እስከ ቀበሌ በአጠቃላይ የመንግስት መዋቅር የሚታየውን የማስፈጸም አቅም ችግሮችን ለመቅረፍ የአቅም ግንባታ ስትራቴጂዎችንና ፕሮግራሞችን የሚያስተባብርና በበላይነት የሚያስፈጽም ተቋማዊ አካል ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የክልሉን አስፈጻሚና ፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 36/1994 እንደገናም ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/95 የአቅም ግንባታ ማስተባበሪያ ቢሮ ሆኖ ሲቋቋም የኢንፎርሚሸን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ከ15 የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች እንደ አንድ አቅም ግንባታ ፕሮግራም ተቀርጾ ሲተገበር ቆይቷል፡፡ Read More

ራዕይ

“በ2030 በክልላችን ውጤታማ የሆኑ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር፣ የማልማት፤ የመፍጠር፣ የማላመድ እና የመጠቀም አቅም ተገንብቶ ማየት”

ተልዕኮ

ለክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣ በመተግበርና በማስፋት ክልላዊ ብሎም አገራዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነዉ፡፡ 

ዕሴቶች

በጎ ህሊናና ቅን ልቦና፣
የስራ ፍቅርና ትጋት፣
ያልተገደበ አስተሳሰብና ምናባዊ ጉዞ፣
ለለውጥ በጋራ መስራት፤
ውጤታችንም ሆነ ውድቀታችን የጋራችን ነው፤
ችግር ፈቺነት፤
የማይረካ የመማር ጥማት፤
ለትውልድ የሚተላለፍ መሠረት፣
ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል፣

 

ዓላማ

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍን በማሳደግ ለፖለቲካዊ፣ ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያለውን አስተዋጽኦ በማጐልበት ክልሉን የፈጣን ልማትና ዕድገት ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ፤

Testimonial

SNNPRS-Science and Information Technology Bureau