• Call Us
  • +25146 2206572

በደቡ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ታረቀኝ መጪውን አዲስ ዓመት በማስመልከት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Mr Habtamuላለፉት ዓመታት ከሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር ሲሰሩ ለነበሩ በክልሉ ለሚገኙ መዋቅሮችና ለቢሮው ሰራተኞች አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን አቶ ሀብታሙ ታረቀኝ ሰጡ፡፡
አቶ ሀብታሙ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫቸው መጪው አዲስ ዓመት የሰላም ፤የብልጽግናና ከመቼውም ጊዜ በላይ ስኬታማ ጉዞን የምንቀጥልበት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በአዲሱ ዓመት ከሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ተደራሽነቱን እያሳደገ ለተገልጋዮቹ ፤ዘመናዊ አሰራርን እየተከተለ ቀልጣፋ አገልግሎቱን በተሻለ ብቃት እና ዘመናዊነትን በተላበሰ መልኩ በመስጠት የስራቸዉ አጋርነቱን አጠናክሮ የሚቀጥልበት፤ለራዕያቸው ስኬት በቅርበት የሚያገለግልበት ዓመት ይሆናል ብለዋል፡፡
አቶ ሀብታሙ ለቢሮው ሰራተኞች ባስተላለፉት መልዕክትም መጪው አዲስ ዓመት የቢሯችንን አገልግሎት በአዳዲስ ቴክኖሎጂ የምናዘምንበት ፤የደንበኞቻችንን ጥያቄ በፈጣን አገልግሎት የምናረካበት ፤ለኢንዱስትሪው የምርምር ስራዎችን በማቅረብ ተወዳዳሪ በመሆን ስኬትን የምንጨብጥበት እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
ስለሆነም የቢሮው ሰራተኞች በታታሪነትና በትጋት ተገልገዮቻችንን በማገልገል ያቀድናቸውን እቅዶች ዳር ለማድረስ እንዲሁም “በ2030 በክልላችን ውጤታማ የሆኑ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር፣ የማልማት፤ የማላመድ እና የመጠቀም አቅም ተገንብቶ ማየት” ራዕያችንን እናሳካ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡