የህወሃት ጁንታ ቡድን ለ27 ዓመታተተ ሲዘርፍና አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጽም መቆየቱ ሳያንሰው በቅርቡ ደግሞ የሃገርን ዳር ድንበር ለማስከበር በቆመው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ አሳፋሪና ከባድ የሀገር ክህደት ወንጀል መፈጸሙ እንዳስቆጣቸው የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች ገልጸዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ባደረጉት ውይይት የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች ከ ወር ደሞዛቸው 50% ለመከላከያ ሰራዊት ለመደገፍ ቃል የገቡ ሲሆን በቀጣይም ሁሉም ሰራተኞች የደም ልገሳ ለማድረግ ፈቃደኝነታቸውን ገልጸዋል፡፡
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሂዲን ሁሴን እያደረግን ያለነው ድጋፍ ለሰራዊታችን የሞራል ስንቅና ወኔ የሚሆነው ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ይህ ድጋፍ ህግን የማስከበር ዘመቻን ባለን አቅም በመደገፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለስኬት አስኪበቃ ድረስ እንዲቀጥልም አቶ ሙሂዲን ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ ደም በመለገስ አስፈላጊ ከሆነም ግንባር ድረስ ሄዶ መደገፍ ከዜጎች የሚጠበቅ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
Copyrights 2020. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU