የዌብ ፖርታል ልማት በከተማችን እንዲጀመር የፌዴራል ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ቢሮ ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸውን የተናገሩት የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ ናቸው።
አክለውም ከንቲባው በከተሞች የዌብ ፖርታል መልማት በኢኮኖሚና ማህበራዊ ትስስር፣ ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ ለመፍጠርና የየከተሞችን አጠቃላይ መረጃ ህብረተሰቡ በማንኛውም ቦታና ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እንዲከታተል ትልቅ ሚና እንዳለውም ገልፀዋል።
የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማፋጠንና በዲጂታል ቴክኖሎጂ እየተካሄደ ያለውን አለም አቀፍ ውድድር በሁሉም መስክ ተፈላጊና ተመራጭ የሆነ ከተማን መመስረትን አላማ በማድረግ የዌብ ፖርታል ልማት ላይ ክልሉ ትኩረት ማድረጉን በምስረታ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገበሬ ጋጌ ተናግረዋል።
በተከፈተው ዌብ ፖርታል መረጃዎች ተጠናክሮ በመደራጀታቸው አበረታች መሆኑን ገልፀው በቀጣይም መረጃዎችን ወቅታዊ በማድረግ ከተማዋ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን አመራሩ ሆነ ባለሙያዎች የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ ይገባልም ብለዋል።
Copyrights 2020. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU