የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኢኮቴ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መንግስቱ በየነ አዲስ የኢኮቴ ኢንኩቤሽን ማዕከል እየተቋቋመ ከሚገኝባቸው ዞኖች ( ወላይታ፣ሀዲያ እና ጋሞ ) የመምሪያ ኃላፊዎች ጋር አስፈላጊው ሙሉ ዝግጅት ተጠናቆ ማዕከላቱን ስራ ማስጀመር ስለሚቻልበት ሁኔታ በቨርቿል ውይይት አድርገዋል፡፡
አቶ መንግስቱ በውይይቱ እያንዳንዱ ዞን ከክልል በተደረገልት የቁሳቁስ ድጋፍ መሰረት ምቹ የሰራ ቦታ ማመቻቸት ፣ ኔትወርክ መዘርጋት እና ስራ አጥ ወጣቶችን የመመልመል ስራ ማከናወን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የኢኮቴ ኢንኩቤሽን ማዕከላቱን የማቋቋም ዓላማ ስራ አጥ ወጣቶችን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ማለትም በኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገና፣ በሶፍት ዌር ልማት እና በኔትወርክ ዝርጋታና ልማት ዘርፍ ገበያው ላይ ተወዳዳሪና ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ለወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር በመሆኑ ዞኖቹ በአፋጣኝ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው በቅርብ ቀን ወደ ስራ እንዲገቡ አሳስበው ውይይቱ በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቋል፡፡
Copyrights 2020. . All Rights Reserved.
Developed by SNNPRS-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU